የዘለዓለም ህይወት ደግሞም ህይወት; አክሊል; ከፍተኛነት; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; የሰለስቲያል ክብር ተመልከቱ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቤተሰብ ለዘለአለም መኖር (ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፲፱–፳፣ ፳፬፣ ፶፭)። ዘለአለማዊ ህይወት እግዚአብሔር ለሰው ከሰጠው ስጦታዎች ታላቁ ነው። አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ, ዮሐ. ፮፥፷፰. እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት, ዮሐ. ፲፯፥፫ (ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፬). መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፣ የዘላለምን ሕይወት ያዝ, ፩ ጢሞ. ፮፥፲፪. ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ ናቸው, ፪ ኔፊ ፪፥፳፯ (ሔለ. ፲፬፥፴፩). ስለመንፈሳዊ ነገር ማሰብ ዘለዓለማዊ ህይወት ነው, ፪ ኔፊ ፱፥፴፱. ወደ ዘለአለም በሚመራው ጠባቡ ጎዳና ላይ ናችሁ, ፪ ኔፊ ፴፩፥፲፯–፳. በክርስቶስ ማመን እና እስከመጨረሻ መፅናት ዘለዓለማዊ ህይወት ነው, ፪ ኔፊ ፴፫፥፬ (፫ ኔፊ ፲፭፥፱). ዘለዓለማዊ ሕይወት ያለው ሰው ሃብታም ነው, ት. እና ቃ. ፮፥፯ (ት. እና ቃ. ፲፩፥፯). ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነውን ዘላለማዊ ህይወት ይኖርሃል, ት. እና ቃ. ፲፬፥፯ (ሮሜ ፮፥፳፫). ጻድቅ በዚህ አለም ሰላም እና በወዲያኛው አለምም ዘለአለማዊ ህይወትን ይቀበላል, ት. እና ቃ. ፶፱፥፳፫. እስከ መጨረሻውም የሚቀጥል የዘለአለም ህይወት አክሊል ይኖረዋል, ት. እና ቃ. ፷፮፥፲፪ (ት. እና ቃ. ፸፭፥፭). ለመቆየት ቢፈቀድላቸው ይቀበሉት የነበሩት፣ ይህን ወንጌል ካለማወቅ የሞቱት ሁሉ የእግዚአብሔር ሰለስቲያል መንግስት ወራሾች ይሆናሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፯፥፯–፱. የእግዚአብሔር ስራና ክብር የሰውን አለሟችነት እና ዘለአለማዊ ህይወትን ማምጣት ነው, ሙሴ ፩፥፴፱. ለታዛዡ ሁሉ እግዚአብሔር ዘለአለማዊ ህይወትን ይሰጣል, ሙሴ ፭፥፲፩.