አመስጋኝ፣ ምስጋናን፣ ምስጋና መስጠት ደግሞም መባረክ፣ የተባረከ፣ በረከት; ማምለክ ተመልከቱ ከእግዚአብሔር ከተቀበልነው በረከቶች የምንሰጠው ምስጋና። ምስጋናን መግለፅ እግዚአብሔርን ያስደስታል፣ እናም እውነተኛ ማምለክ ምስጋና በተጨማሪ አለው። ለጌታ ለሁሉም ነገሮች ምስጋና መስጠት ይገባናል። እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው, መዝ. ፺፪፥፩. በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ, መዝ. ፺፭፥፩–፪. አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ, መዝ. ፻. ማመስገንን አትተው, ኤፌ. ፩፥፲፭–፲፮. የምታመሰግኑም ሁኑ, ቄላ. ፫፥፲፭. በረከትና ክብር ጥበብም ምስጋናም ውዳሴም ኃይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን, ራዕ. ፯፥፲፪. በረከትና ክብር ምስጋናም ውዳሴም ለአምላካችን ይሁን, ሞዛያ ፪፥፲፱–፳፩. በየቀኑ በምስጋና ኑሩ, አልማ ፴፬፥፴፰. ጠዋት ከመኝታህ በምትነቃበት ጊዜ ልብህ ሁሉ እግዚአብሔርን በማመስገን ይሞላ, አልማ ፴፯፥፴፯. ሁሉንም ነገሮች በጸሎትና በምስጋና አድርጉ, ት. እና ቃ. ፵፮፥፯. ምስጋናዎችን ለእግዚአብሔር መስጠት አለባችሁ, ት. እና ቃ. ፵፮፥፴፪. ምስጋና በመስጠት እነዚህን ነገሮች አድርጉ, ት. እና ቃ. ፶፱፥፲፭–፳፩. ከጌታ እጅ ለሁሉም ነገሮች ምስጋና ባለው ልብ በረከትን ተቀበለ, ት. እና ቃ. ፷፪፥፯. ሁሉንም ነገሮች በምስጋና የሚቀበል ባለክብር ይሆናል, ት. እና ቃ. ፸፰፥፲፱. በሁሉም ነገሮች ምስጋናዎች ስጡ, ት. እና ቃ. ፺፰፥፩ (፩ ተሰ. ፭፥፲፰). ጌታን በምስጋና ጸሎትና በምስጋና አምልኩ, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፳፰.