የጥናት እርዳታዎች
ሔለማን፣ የሔለማን ልጅ


ሔለማን፣ የሔለማን ልጅ

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የኔፋውያንን ህዝቦች ያስተማረው ነቢይ እና መዝገብ ጠባቂ። እርሱም የታናሹ አልማ የልጅ ልጅ እና በሁሉም ነገሮች ላይ ሀይል የተሰጠው ኔፊ አባት ነበር። ከልጁ ኔፊ ጋር፣ ሔለማን መፅሐፈ ሔለማንን ጻፈ።

መፅሐፈ ሔለማን

ምዕራፍ ፩–፪ ታላቅ የፖለቲካ ችግርን ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፫–፬ ሔለማን እና የኔፋውያን ሰራዊት ዋና ሻምበል የሆነው ሞሮኒሀ በመጨረሻም ለጊዜ ሰላም ለመመስረት ቻሉ። ነገር ግን፣ እነዚህ ጥሩ ሰዎች የእነርሱ መሪዎች ቢሆኑም፣ ህዝቦቹ በክፋት ጨመሩ። በሔለማን ፭፥፩–፮፥፲፬ ውስጥ ኔፊ አያቱ አልማ እንዳደረገው ህዝቡን ለማስተማር የፍርድ ወንበሩን ተወ። ለጊዜው ህዝቡ ንስሀ ገባ። በሔለማን ፮፥፲፭–፲፪፥፳፮ ውስጥ ግን የኔፋውያን ህዝብ ክፉ ሆኑ። በመጨረሻው ምዕራፍ ፲፫–፲፮ ስለአዳኝ መወለድ እና መሰቀል እና እነዚህን ድርጊቶች ስለሚያሳዩት ምልክቶች አስቀድሞ ስለተናገረ ላማናውያን ሳሙኤል ስለተባለው ነቢይ አስደናቂ ታሪክን ይዘዋል።