የጥናት እርዳታዎች
ጋብቻ፣ መጋባት


ጋብቻ፣ መጋባት

በወንድ እና ሴት መካከል ባልና ሚስት የሚያደርጓቸው ህጋዊ ቃል ኪዳን ወይም ውል። እግዚአብሔር ጋብቻን መደበ (ት. እና ቃ. ፵፱፥፲፭)።

አዲስ እና ዘለአለማዊ የጋብቻ ቃል ኪዳን

በወንጌል ህግ ስር እና በቅዱስ ክህነት ስር የተፈጸመ ጋብቻ ለስጋዊ ህይወት እና ለዘለአለም ነው። እንደዚህ በቤተመቅደስ ጋብቻ የተሳሰሩ ብቁ የሆኑ ወንዶች እና ሴቶች ለዘለአለም በሙሉ እንደ ባልና ሚስት ለመቀጠል ይችላሉ።

በሀይማኖቶች መካከል መጋባት

የሀይማኖት እምነት እና ልምምድ ልዩነት ያላቸው ወንድና ሴት መጋባት።

ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት

አንድ ባል ከሁለት ወይም ተጨማሪ ሚስቶች ጋር መጋባት። በራዕይ እግዚአብሔር ከዚህ ሌላ እንዲሆን ካላዘዘ በስተቀር፣ አንድ ሰው አንድ ሚስት ብቻ ማግባቱ ህጋዊ ነው (ያዕቆ. ፪፥፳፯–፴)። ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት በብሉይ ኪዳን ውስጥ በራዕይ፣ እናም ዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያን ውስጥ የክህነት ቁልፎችን በያዘ ነቢይ አመራር መሰረት የሚደረግ ነበር (ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፴፬–፵፣ ፵፭)። በቤተክርስቲያኗ አሁን የሚደረግ አይደለም (አ.አ. ፩)፤ ዛሬ፣ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነት ጋር የሚስማማ አይደለም።