ንጹህ እና ርኩስ
በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ጌታ ለሙሴ እና ለጥንት እስራኤላውያን አንዳንድ ምግቦች ንጹህ፣ ወይም በሌላ አባባል፣ ለመብላት ብቁ እንደሆኑ ገለጸላቸው። እስራኤላውያን በንጹህ እና በርኩስ ምግቦች መካከል የሰጡት ልዩነት በሀይማኖታቸውና በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ታላቅ ተፅዕኖ ነበራቸው። አንዳንድ እንስሳት፣ ወፎች፣ እና አሳ ለምግብ ንጹህ እና ተቀባይ ነበሩ፣ ሎሎችም ርኩስ እና የተከለከሉ ነበሩ (ዘሌዋ. ፲፩፤ ዘዳግ. ፲፬፥፫–፳)። አንዳንድ በሽተኛ ሰዎች እንደ ርኩስ ይቆጠሩ ነበር።
በመንፈሳዊ አመለካከት፣ ንጹህ መሆን ከኃጢያት እና ከኃጢያታዊ ፍላጎቶች ነጻ መሆን ነው። በዚህ አስተያየትም ያሉ ምግባረ ጥሩና ንጹህ ልብ ያለውን ሰው ይገልጻል (መዝ. ፳፬፥፬)። የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ህዝቦች ንጹህ ለመሆን ልዩ መመሪያ አላቸው (፫ ኔፊ ፳፥፵፩፤ ት. እና ቃ. ፴፰፥፵፪፤ ፻፴፫፥፭)።