መጠበቅ፣ ጠባቂ ደግሞም ማስጠንቀቅ፣ ማስጠንቀቂያ ተመልከቱ ንቁ መሆን፣ መጠበቅ። የሚጠብቅና ታዛዥ የሆነ እናም የተሰጋጀ ሰው። ጠባቂዎች በጌታ ወኪሎች ለሌሎች ጥቅም ልዩ ሀላፊነት እንዲኖራቸው የተጠሩ መሪዎች ናቸው። መሪዎች እንዲሆኑ የተጠሩትም በአለም ላሉት ሌሎች ጠባቂ የመሆን ሀላፊነት አላቸው። ጠባቂ አድርጌሃለሁ, ሕዝ. ፫፥፲፯–፳፩. የማስጠንቀቂያ ድምፅ የሚያነሱ ጠባቂዎች ነፍሳቸውን ያድናሉ, ሕዝ. ፴፫፥፯–፱. ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ, ማቴ. ፳፬፥፵፪–፵፫ (ማቴ. ፳፭፥፲፫; ማር. ፲፫፥፴፭–፴፯; ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፲–፲፩). ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ, ማቴ. ፳፮፥፵፩ (፫ ኔፊ ፲፰፥፲፭፣ ፲፰). ራሳችሁን፣ እናም ሀሳባችሁን፣ እናም ቃላችሁን፣ እናም ድርጊታችሁን የማታስተውሉ ከሆናችሁ፣ መጥፋት ይገባችኋል, ሞዛያ ፬፥፴. አልማ ቤተክርስቲያኗን እንዲመሩና እንዲቆጣጠሩ ካህናትን እና ሽማግሌዎችን ሾመ, አልማ ፮፥፩. አዳኝን የማይጠብቀውም ተለይቶ ይጠፋል, ት. እና ቃ. ፵፭፥፵፬. ኤጲስ ቆጶስና ሌሎች ቤተክርቲያኗን እንዲጠብቁ ተጠሩት እና ተሾሙ, ት. እና ቃ. ፵፮፥፳፯. ጌታ በወይን አትክልት ስፍራው ላይ ጠባቂዎች አስቀመጠ, ት. እና ቃ. ፻፩፥፵፬–፶፰.