መፍጠር፣ ፍጥረት ደግሞም መጀመሪያ; ምድር; ኢየሱስ ክርስቶስ; የመንፈስ ፍጥረት; የሰንበት ቀን ተመልከቱ ማደራጀት። እግዚአብሔር፣ በልጁ በኩል በመስራት፣ በፍጥረት ውስጥ ያሉትን ንጥረ ነገሮች በማደራጀት ሰማያትንና ምድርን ሰራ። የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ሰውን በመልካቸው ፈጠሩ (ሙሴ ፪፥፳፮–፳፯)። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ, ዘፍጥ. ፩፥፩. ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር, ዘፍጥ. ፩፥፳፮ (ሙሴ ፪፥፳፮–፳፯; አብር. ፬፥፳፮). ሁሉ በእርሱ ሆነ, ዮሐ. ፩፥፫፣ ፲. በሰማይ ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል, ቄላ. ፩፥፲፮ (ሞዛያ ፫፥፰; ሔለ. ፲፬፥፲፪). እግዚአብሔር አለማትን በልጁ ፈጠረ, ዕብ. ፩፥፪. በመጀመሪያ ሰው ተፈጠረ, ሞዛያ ፯፥፳፯. ሰማያትንና ምድርን እንዲሁም ሁሉንም ነገሮች ፈጠርኩኝ, ፫ ኔፊ ፱፥፲፭ (ሞር. ፱፥፲፩፣ ፲፯). ሁሉም ሰዎች በመጀመሪያ በራሴ ምስል ተፈጥረዋል, ኤተር ፫፥፲፭. ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ, ት. እና ቃ. ፲፬፥፱. ሰውን፣ ወንድንና ሴትን፣ በመልኩ ፈጠረ, ት. እና ቃ. ፳፥፲፰. ለመቁጠር የማይቻል አለሞችንም ፈጠርኩኝ, ሙሴ ፩፥፴፫. በአንድያ ልጄ ሰማይን ፈጠርኩኝ, ሙሴ ፪፥፩. እኔ እግዚአብሔር አምላክም የተናገርኩባቸውን ነገሮች ሁሉ ከምድር ፊት በፍጥረታዊ አካል ከመፈጠራቸው በፊት በመንፈሳዊ አካል ፈጥሬአቸዋለሁ, ሙሴ ፫፥፭. እንደዚህ አይነት ሚልዮን ምድሮችን የአንተን ለፈጠርካቸው የመቆጠሪያ መጀመሪያም አይሆንም, ሙሴ ፯፥፴. አምላኮች ወረዱና ሰማያትን መሰረቱም ሰሩም, አብር. ፬፥፩.