የጥናት እርዳታዎች
ሽማግሌ


ሽማግሌ

ሽማግሌ የሚባለው ቃል በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች ተጠቅመውበታል። በብሉይ ኪዳን ውስጥ በብዙ ጊዜ በጎሳ ውስጥ የሚገኙትን፣ በመንግስት ጉዳዮች የሚመኩበትን፣ ሽማግሌዎች ይጠቅሣል (ዘፍጥ. ፶፥፯ኢያ. ፳፥፬ሩት ፬፥፪ማቴ. ፲፭፥፪)። እድሜአቸው እና አጋጣሚያቸው የእነርሱን ምክር ታላቅ ዋጋ ይሰጠዋል። ቦታቸውም የክህነት ጥሪ መሆኑ አስፈላጊም አልነበረም።

በብሉይ ኪዳን ጊዜዎች በመልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ የተሾሙ ሽማግሌዎችም ነበሩ (ዘፀአ. ፳፬፥፱–፲፩)። በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ ሽማግሌዎች በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እንደ ክህነት ሀላፊነቶች ተጠቅሰዋል (ያዕ. ፭፥፲፬–፲፭)። በኔፋውያን መካከል በክህነት ስልጣን ውስጥ እንደ ሽማግሌዎች የተሾሙም ነበሩ (አልማ ፬፥፯፣ ፲፮ሞሮኒ ፫፥፩)። በዚህ ዘመን ውስጥ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ የተሾሙ የመጀመሪያ ሽማግሌዎች ነበሩ (ት. እና ቃ. ፳፥፪–፫)።

ሽማግሌ አሁን የመልከ ጼዴቅ ክህነት ባለስልጣን ለሆኑት ሁሉ የተሰጠ ስም ነው። ለምሳሌ፣ ወንድ ሚስዮኖች እንደ ሽማግሌዎች ነው የሚጠሩት። ደግሞም፣ ሐዋሪያ ሽማግሌ ነው፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባላትን ወይም የሰባዎች ቡድን አባላትን በዚህ ርዕስ መናገር ትክክለኛ ነው (ት. እና ቃ. ፳፥፴፰፩ ጴጥ. ፭፥፩)። በአሁን ቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተሾሙ ሽማግሌዎች ሀላፊነቶች በኋለኛው ቀን ራዕይ ተሰጥተዋል (ት. እና ቃ. ፳፥፴፰–፵፭፵፪፥፵፬፵፮፥፪፻፯፥፲፪)።