ማክበር ደግሞም ክብር; ፍርሀት ተመልከቱ ለቅዱስ ነገሮች ጥልቅ ክብር መኖር፤ ድንቅ በቅዱስ ምድር ላይ ስለቆመ፣ ጌታ ሙሴን ጫማዎቹን እንዲያወልቅ አዘዘው, ዘፀአ. ፫፥፬–፭. እግዚአብሔር ክቡር ነው፤ ግሩም ነው, መዝ. ፹፱፥፯. እግዚአብሔርን በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን እናገልግል, ዕብ. ፲፪፥፳፰. ሞሮኒ በመሬት ላይ ሰገደ፣ በኃይል ፀለየ, አልማ ፵፮፥፲፫. ህዝቡ በምድር ላይ ወደቁ እናም ለክርስቶስ ሰገዱ, ፫ ኔፊ ፲፩፥፲፪–፲፱. እራሱን ዝቅ ያድርግ, ት. እና ቃ. ፭፥፳፬. በዙፋኑ ፊትም ሁሉም ነገሮች በትህትና ይሰግዳሉ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፺፫. የተቀበላችሁትን እንደተራ ስለተቀበላችሁት፣ አዕምሮአችሁ ባለማመን ምክንያት ጨልሞባችሁ ነበር, ት. እና ቃ. ፹፬፥፶፬–፶፯. ጉልበት ሁሉ ይንበረከካል ምላስም ሁሉ ይናዘዛል, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፬. ለኃያል ጌታ ስም ክብር ወይም አምልኮ፣ ቤተክርስቲያኗ ክህነትን የመልከ ጼዴቅ ክህነት ወይም በመልከ ጼዴቅ ስም ጠሩት, ት. እና ቃ. ፻፯፥፬. ጌታ በቤቱ ለሚያከብሩት ሁሉ በረከቶች ያፈሣል, ት. እና ቃ. ፻፱፥፳፩.