ሕመም፣ ታማሚነት በሽታ ወይን ህመም ያለው። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ አንዳንዴ የስጋዊ ህመም የመንፈሳዊ ደህንነት ያለመኖር ምልክት ሆኖ ያገለግላል (ኢሳ. ፩፥፬–፯፤ ፴፫፥፳፬)። ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ እፈውስሃለሁ, ፪ ነገሥ. ፳፥፩–፭ (፪ ዜና ፴፪፥፳፬; ኢሳ. ፴፰፥፩–፭). ኢየሱስም በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ ይዞር ነበር, ማቴ. ፬፥፳፫–፳፬ (፩ ኔፊ ፲፩፥፴፩; ሞዛያ ፫፥፭–፮). ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም, ማቴ. ፱፥፲–፲፫ (ማር. ፪፥፲፬–፲፯; ሉቃ. ፭፥፳፯–፴፪). ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ, ያዕ. ፭፥፲፬–፲፭. ክርስቶስ የህዝቡን ህመምና በሽታ በራሱ ላይ ይወስዳል, አልማ ፯፥፲–፲፪. ኢየሱስ በኔፋያን መካከል ሁሉንም በሽተኞንን ፈወሰ, ፫ ኔፊ ፳፮፥፲፭. በደግነት፣ በቅጠላቅጠል እና በለስላሳ ምግብ የታመመውን ይመግብ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፵፫ (አልማ ፵፮፥፵). በሁሉም ነገሮችም ድሀውን የተሰቃየውን አስታውሱ, ት. እና ቃ. ፶፪፥፵. በታመሙትም ላይ እጆችህን ጫን፣ እናም ይድናሉ, ት. እና ቃ. ፷፮፥፱.