መስበክ ደግሞም ወንጌል; የሚስዮን ስራ ተመልከቱ የወንጌል መሰረታዊ መመሪያ ወይም የትምህርት ማስተዋልን በይበልጥ ለማቅረብ የሚሰጥ መልእክት። እግዚአብሔር ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛል, ኢሳ. ፷፩፥፩ (ሉቃ. ፬፥፲፮–፳፩). ተነሥተህ ወደ ነነዌ ሂድ፥ ስበክላት, ዮና. ፫፥፪–፲. ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ ይሰብክ ጀመር, ማቴ. ፬፥፲፯. ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ, ማር. ፲፮፥፲፭. የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን, ፩ ቆሮ. ፩፥፳፪–፳፬. በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው, ፩ ጴጥ. ፫፥፲፱. በጌታ ፍርሃት ያለማቋረጥም ይጠበቁ ዘንድ ካነሳሳቸው በስተቀር ምንም የለም, ኢኖስ ፩፥፳፫. ንስሃንና እምነትን ካልሆነ በቀር ምንም እንዳያስተምሩ አዘዛቸው, ሞዛያ ፲፰፥፳. የቃሉ መሰበክ ህዝቡ ትክክለኛውን እንዲሰራ የሚመራ ታላቅ ዝንባሌ አለው, አልማ ፴፩፥፭. እስከምትጠራ ድረስ እንድትሰብክ እንደተጠራህ አታስብ, ት. እና ቃ. ፲፩፥፲፭. ካልተሾመ በስተቀር፣ ለማንም ወንጌሌን እንዲሰብክ እንዲገንባ አይሰጠውም, ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፩. ወንጌል ለእያንዳንድ ሕዝብ ይሰበክ, ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፴፯. ወንጌሉ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ መሰበክ ጀመረ, ሙሴ ፭፥፶፰.