ዐይነ-እርግብ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ (፩) የታቦትን ወይም የቤተመቅደስን ክፍሎች የሚያለያይ መከፋፈያ፣ (፪) የእግዚአብሔር እና የሰው መለያየት ምልክት፣ (፫) ሰዎች ፊታቸውን ወይም ጭንቅላታቸውን ለመሸፈን የሚጠቀሙበት ጨረቅ ወይም (፬) የሰዎችን የቅድመ ምድር ህይወት ትዝታን የሚዘጋ በእግዚአብሔር የተሰጠ ዝንጉነት። መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ, ዘፀአ. ፳፮፥፴፫. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ, ማቴ. ፳፯፥፶፩ (ማር. ፲፭፥፴፰; ሉቃ. ፳፫፥፵፭). ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን, ፩ ቆሮ. ፲፫፥፲፪. እርሱም ያለማመን ጥቁር መጋረጃው ከአዕምሮው እንደተወሰደ ያውቅ ነበር, አልማ ፲፱፥፮. የያሬድ ወንድም በመጋረጃው ውስጥ ከመመልከት ሊጠበቅ አልቻለም, ኤተር ፫፥፲፱ (ኤተር ፲፪፥፲፱). መጋረጃውም ይገፈፋል እናም አይታችሁኝ, ት. እና ቃ. ፷፯፥፲ (ት. እና ቃ. ፴፰፥፰). ቤተመቅደሴን የሚሸፍነው መጋረጃ ይወልቃል, ት. እና ቃ. ፻፩፥፳፫. መጋረጃው ከአዕምሮዎቻችን ተወገደ, ት. እና ቃ. ፻፲፥፩. የጭለማም መጋረጃ ምድርን ይሸፍናል, ሙሴ ፯፥፷፩.