መንፈሳዊ ጭለማ ደግሞም ክፉ፣ ክፋት ተመልከቱ ጥፋተኛነት ወይም ስለመንፈሳዊ ነገሮች አላዋቂነት። ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ, ኢሳ. ፭፥፳ (፪ ኔፊ ፲፭፥፳). ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል, ኢሳ. ፷፥፪. ኢየሱስ ብርሃኑም በጨለማና ተቀምጠው ላሉት ያበራል, ሉቃ. ፩፥፸፱. ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም, ዮሐ. ፩፥፭ (ት. እና ቃ. ፵፭፥፯). እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ, ሮሜ ፲፫፥፲፪. ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ, ኤፌ. ፭፥፰–፲፩. ስላልጠየቃችሁ፣ ወይም ስላላንኳኳችሁ ነው፤ ስለሆነም፣ ወደ ብርሃኑ አልመጣችሁም፣ ነገር ግን በጨለማው ትጠፋላችሁ, ፪ ኔፊ ፴፪፥፬. ሰይጣን የጨለማ ስራን ያሰራጫል, ሔለ. ፮፥፳፰–፴፩. የጨለማ ሀይሎች በምድር ላይ ይሰራጫል, ት. እና ቃ. ፴፰፥፰፣ ፲፩–፲፪. አለም በሙሉ በጨለማና በኃጢያት ስር ይቃሰታሉ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፵፱–፶፬. ለክብሬ ዐይናችሁ ቀና ብትሆን፣ በእናንተም ምንም ጭለማ አይኖርም, ት. እና ቃ. ፹፰፥፷፯. እንደዚህም የጭለማ ስራዎች በሰው ልጆች ሁሉ መካከል መሳካት ጀመረ, ሙሴ ፭፥፶፭.