ቅድስና ደግሞም ማፅደቅ፣ ከበደል ነጻ መሆን; ቅዱስ; ንጹህ፣ ንጹህነት; ኢየሱስ ክርስቶስ; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ ተመልከቱ መንፈሳዊና የስነምግባር ፍጹምነት። ቅድስና የሰው ልብን እና አላማ ንጹህነትን ያመለክታል። በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ከኃጢያት በንጻት፣ ንጹህ፣ የጸዳ፣ እና ቅዱስ መሆን (ሙሴ ፮፥፶፱–፷)። እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ ለመዳን መርጦአችኋል, ፪ ተሰ. ፪፥፲፫. የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል, ዕብ. ፲፥፲. ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ መከራን ተቀበለ, ዕብ. ፲፫፥፲፪. ሊቀ ካህናት በበጉ ደም ልብሳቸው እስከሚነጣ ታጥበው ነበር, አልማ ፲፫፥፲–፲፪. ለእግዚአብሔር በፍቃድ ልቦቻቸው ለሚሰጡት ቅድስና ይመጣል, ሔለ. ፫፥፴፫–፴፭. መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ትቀደሱ ዘንድ ንስሀ ግቡ, ፫ ኔፊ ፳፯፥፳. በጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በኩል የሚገኘው ቅድስና ትክክል እና እውነተኛ ነው, ት. እና ቃ. ፳፥፴፩. አባሎቹ በጌታ ፊት በቅድስና በመሄድ ብቁ መሆናቸውን ያሳዩ, ት. እና ቃ. ፳፥፷፱. ኢየሱስ አለምን ለመቀደስ መጣ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፵፩. አዕምሮአችሁ ለእግዚአብሔር የቀኑ እንዲሆኑ ራሳችሁን ቀድሱ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፷፰. የጌታ ቤት የቅድስናህ ቦታ ነው, ት. እና ቃ. ፻፱፥፲፫. የቅድስና ሰው ከእግዚአብሔር ስሞች አንዱ ነው, ሙሴ ፮፥፶፯ (ሙሴ ፯፥፴፭).