የፓትሪያርክ በረከቶች ደግሞም ሟች አባት; ወንጌል ሰባኪ; የአባቶች አለቃ፣ ፓትሪያርክ ተመልከቱ በተሾሙ ፓትሪያርኮች ለብቁ የቤተክርስቲያኗ አባላት የሚሰጡ በረከቶች። የፓትሪያርክ በረከቶች በረከቱን ለሚቀበለው ሰው የጌታን ምክር ይይዛሉ እናም ሰው በእስራኤል ቤት ውስጥ ያላቸውን ዝርያ ይገልጻሉ። አባቶች እንደቤተሰቦቻቸው አለቃ ልዩ በረከቶችን ለመስጠት ይችላሉ፣ ነገር ግን እንደዚህ አይነት በረከቶች አይመዘገቡም ወይም በቤተክርስቲያኗ አይጠበቁም። እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው, ዘፍጥ. ፵፰፥፲፬. ያዕቆብ ልጆቹን እና ዘሮቹን ባረከ, ዘፍጥ. ፵፱. ሌሂ ትውልዶቹን ባረከ, ፪ ኔፊ ፬፥፫–፲፩.