የህይወት ዛፍ ደግሞም ዔድን ተመልከቱ በዔድን ገነት እና በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ የሚገኝ ዛፍ (ዘፍጥ. ፪፥፱፤ ራዕ. ፪፥፯)። በሌሂ ህልም ውስጥ የህይወት ዛፍ የእግዚአብሔርን ፍቅር የወከለ እናም ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ነበር (፩ ኔፊ ፰፤ ፲፩፥፳፩–፳፪፣ ፳፭፤ ፲፭፥፴፮)። ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ጠበቁ, ዘፍጥ. ፫፥፳፬ (አልማ ፲፪፥፳፩–፳፫; ፵፪፥፪–፮). ዮሐንስ የሕይወት ዛፍ አየ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ, ራዕ. ፳፪፥፪. ሌሂ የህይወት ዛፍን አየ, ፩ ኔፊ ፰፥፲–፴፭. ኔፊ አባቱ ያየውን ዛፍ አየ, ፩ ኔፊ ፲፩፥፰–፱. የብረት በትር ወደ ህይወት ዛፍ ይመራል, ፩ ኔፊ ፲፩፥፳፭ (፩ ኔፊ ፲፭፥፳፪–፳፬). ከህይወት ዛፍ የሚለያይ አሰቃቂ ገደል ነበር, ፩ ኔፊ ፲፭፥፳፰፣ ፴፮. የተከለከለውም ፍሬ እንደ ህይወት ዛፍ ተቃራኒ መኖሩ አስፈላጊ ነበር, ፪ ኔፊ ፪፥፲፭. ወደ ጌታ ኑ እናም ከህይወት ዛፍም ፍሬ ትካፈላላችሁ, አልማ ፭፥፴፬፣ ፷፪. የመጀመሪያ ወላጆቻችን የህይወት ዛፍን መመገብ ቢችሉ ኖሮ ለዘለዓለም ደስታ የሌላቸው በሆኑ ነበር, አልማ ፲፪፥፳፮. ቃሉን የማትንከባከቡት ከሆነ፣ ከህይወት ዛፍ ፍሬ በጭራሽ መቅጠፍ አትችሉም, አልማ ፴፪፥፵. ጌታ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ ተከለ, ሙሴ ፫፥፱ (አብር. ፭፥፱). ከህይወት ዛፍ በልተው እስከዘለአለም እንዳይኖሩ ዘንድ እግዚአብሔር አዳምን ከኤደን አስወጣው, ሙሴ ፬፥፳፰–፴፩.