የጥናት እርዳታዎች
ዕዝራ


ዕዝራ

አንዳንድ አይሁዶችን ከባቢሎን ምርኮ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው የብሉይ ኪዳን ካህንና ጸሀፊ (ዕዝ. ፯–፲ነሀ. ፰፲፪)። በ፬፻፹፭ ም.ዓ. ከፋርስ ንጉስ አርጤክስስ ለመሄድ የሚፈልገውን ማንኛውንም የአይሁድ ስደተኛ ወደ ኢየሩሳሌም ለመውሰድ ፈቃድ አገኘ (ዕዝ. ፯፥፲፪–፳፮)።

ከዕዝራ ጊዜ በፊት፣ “ህግ” ተብለው የሚጠሩትን የተጻፉ ቅዱሣት መጻህፍትን በማንበብ ላይ ካህናት ሙሉ ስልጣን ነበራቸው። ዕዝራ ቅዱስ መጻህፍቱ ለሁሉም አይሁዶች ለመገኘት እንዲችሉ ረዳ። “የህጉ መፅሐፍ” መነበብ የአይሁዳ ሀገር ህይወት ዋና ክፍል ሆነ። ከዕዝራ ትምህርቶች ታላቁ ቢኖር የጌታን ህግ ለመፈለግ፣ ለማክበር፣ እና ለሌሎች ለማስተማር ልቡን ያዘጋጀበት የእራሱ ምሳሌ ነበር (ዕዝ. ፯፥፲)።

መፅሕፈ ዕዝራ

ምዕራፍ ፩–፮ ዕዝራ በኢየሩሳሌም ከመድረሱ ከስልሳ እስከ ሰማኒያ አመት በፊት የነበሩትን፣ በ፭፻፴፯ ም.ዓ. የቂሮስ አዋጅ እና በዘሩባቤል ስር የአይሁዳ መመለስ አይነት ድርጊቶችን ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፯–፲ ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም እንዴት እንደተመለሰ ያሳያሉ። እርሱ እና ከእርሱ ጋር የሚጓዙት ለጥበቃ ጾሙም ጸለዩም። በኢየሩሳሌም በዘሩባቤል ስር ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱና ከቃል ኪዳን ውጪ ሴቶችን ያገቡና በዚህም እራሳቸውን ያረከሱ ብዙ አይሁዶችን አገኙ። ዕዝራ ለእነርሱ ጸለየ እና ባለቤቶቻቸውን እንዲፈቱ በቃል ኪዳን ስር አደረጋቸው። የዕዝራ የኋለኛ ታሪክም በመፅሐፈ ነህምያ ውስጥ ይገኛል።