ልሙኤል ደግሞም ላማናውያን; ላማን; ሌሂ፣ የኔፊ አባት ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ የሌሂ ሁለተኛ ወንድ ልጅ እና ከኔፊ ታላቅ ወንድሞች አንዱ። ኔፊን ለመቃወም ከወንድሙ ጋር አንድ ሆነ። ሌሂ ልሙኤልን እንደሸለቆ የማይነቃነቅ እንዲትሆን ገሰጸው, ፩ ኔፊ ፪፥፲. ኔፊ ላይ ተናደደ፣ የላማንን ቃላት አድምጦአል, ፩ ኔፊ ፫፥፳፰. ልሙኤላውያን ከላማናውያን ጋር ተጨምረው ነበር, ያዕቆ. ፩፥፲፫–፲፬ (አልማ ፵፯፥፴፭).