መልካሙ እረኛ ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ ኢየሱስ ክርስቶስ መልካሙ እረኛ ነው። በምሳሌም፣ ተከታዮቹ ኢየሱስ እንደሚጠብቃቸው በጎች ናቸው። እግዚአብሔር እረኛዬ ነው, መዝ. ፳፫፥፩. መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል, ኢሳ. ፵፥፲፩. በጎቼን እፈልጋለሁ, ሕዝ. ፴፬፥፲፪. መልካም እረኛ እኔ ነኝ, ዮሐ. ፲፥፲፬–፲፭. ኢየሱስ ለበጎች ትልቅ እረኛ ነው, ዕብ. ፲፫፥፳. በጎቹንም ይቆጥራል፣ እናም እነርሱ ያውቁታል, ፩ ኔፊ ፳፪፥፳፭. መልካሙ እረኛ እናንተን ይጣራል እላችኋለሁ፣ ይህም ክርስቶስ ነው, አልማ ፭፥፴፰፣ ፷. አንድ መንጋ፣ እናም እረኛውም አንድ ይሆናል, ፫ ኔፊ ፲፭፥፳፩ (ዮሐ. ፲፥፲፮).