ሙሴ
እስራኤላውያንን ከግብጻዊ ባርነት ያወጣ እና ከእግዚአብሔር የተገለጹ የሀይማኖት፣ የህብረተሰባዊ፣ እና የምግብ ህግጋት የሰጣቸው የብሉይ ኪዳን ነቢይ።
የሙሴ አገልግሎት ከስጋዊ ህይወቱ በኋላም የተዘረጋ ነው። ጆሴፍ ስሚዝ ከኤልያስ ጋር ወደ መቀየሪያ ተራራ ላይ እንደመጣ እና ለጴጥሮስ፣ ለያዕቆብና፣ ለዮሐንስ የክህነት ቁልፎችን እንደሰጠ አስተምሯል (ማቴ. ፲፯፥፫–፬፤ ማር. ፱፥፬–፱፤ ሉቃ. ፱፥፴፤ ት. እና ቃ. ፷፫፥፳፩)።
በሚያዝያ ፫፣ ፲፰፻፴፮ (እ.አ.አ.) ሙሴ በጆሴፍ ስሚዝ እና በኦሊቨር ካውደሪ በከርትላንድ ኦሀዮ ቤተመቅደስ ውስጥ ታየ እናም በእነርሱም ላይ እስራኤልን የመሰብሰብ ቁልፎችን ሰጠ (ት. እና ቃ. ፻፲፥፲፩)።
የኋለኛው ቀን ራዕይ ሙሴን በሚመለከት ብዙ ይናገራሉ። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል፣ እናም በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ስለአገልግሎቱ (ት. እና ቃ. ፹፬፥፳–፳፮) እናም ከአማቱ ዮቶር ክህነትን እንደተቀበለ (ት. እና ቃ. ፹፬፥፮) እንማራለን።
የኋለኛው ቀን ራዕይ ደግሞም በእስራኤል ልጆች መካከል ስለነበረው አገልግሎቱ የመፅሀፍ ቅዱስ ታሪክን ያረጋግጣል እናም የብሉይ ኪዳን የመጀመሪያ አምስት መፅሐፎች ጸሀፊም እንደሆነ ያረጋግጣል (፩ ኔፊ ፭፥፲፩፤ ሙሴ ፩፥፵–፵፩)።
መፅሐፈ ሙሴ
በየታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ የኦሪት ዘፍጥረት የመጀመሪያ ሰባት ምዕራፎችን ጆሴፍ ስሚዝ በመነሳሳት የተረጎማቸው የሚገኝበት መፅሐፍ።
ምዕራፍ ፩ ሙሴ የደህንነት አላማን በሙሉ የገለፀለትን እግዚአብሔር ያየበትን ራዕይ ይገልጻል። ምዕራፍ ፪–፭ የፍጥረት እና የሰው ውድቀት ታሪክ ናቸው። ምዕራፍ ፮–፯ የሔኖክ እና በምድር አገልግሎቱ ራዕይን የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፰ የኖኅ እና የታላቅ ጎርፍ ራዕይን የያዘ ነው።
የሙሴ አምስት መጻህፍት
የብሉይ ኪዳን የመጀመሪያ አምስት መጻህፍት የሙሴ መፅሐፎች ተብለው ይጠራሉ። ኔፊ ከላባን የወሰደው የናስ ሰሌዳ የሙሴ መጻህፍትን የያዘ ነበር (፩ ኔፊ ፭፥፲፩)።