ሔለማን፣ የአልማ ልጅ ደግሞም አልማ፣ የአልማ ወንድ ልጅ; አንቲ-ኔፊ-ሌሂ; የሔለማን ልጆች ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የአልማ ልጅ አልማ ታላቅ ልጅ (አልማ ፴፩፥፯)። ሔለማን ነቢይ እና የጦር ሀይል መሪ ነበር። አልማ የህዝቡን መዝገቦች እና የያሬዳውያን ሰሌዳዎችን ለልጁ ለሔለማን ሰጠ, አልማ ፴፯፥፩–፪፣ ፳፩. አልማ ሔለማንን የህዝቡን ታሪክ በመጻፍ እንዲቀጥል አዘዘው, አልማ ፵፭–፷፪. ሔለማን ቤተክርስቲያኗን እንደገና መሰረተ, አልማ ፵፭፥፳፪–፳፫. ሁለት ሺህ አሞናውያን ጀግናዎች ሔለማን መሪአቸው እንዲሆን ፈለጉት, አልማ ፶፫፥፲፱፣ ፳፪. ሔለማን እና ብላቴና አሞናውያን ከላማናውያን ጋር ተዋጉ እናም በእምነትም ዳኑ, አልማ ፶፯፥፲፱–፳፯.