የጥናት እርዳታዎች
ዕንባቆም


ዕንባቆም

በይሁዳ ውስጥ ምናልባት በዮአኪን አገዛዝ ዘመን ስለህዝቡ ኃጢያተኛነት የተናገረ የብሉይ ኪዳን ነቢይ (በ፮፻ ም.ዓ. አካባቢ)።

ትንቢተ ዕንባቆም

ምዕራፍ ፩ በኤርምያስ ፲፪ እና በትምህርት እና ቃል ኪዳን ፻፳፩ ውስጥ እንደሚገኙት አይነት በጌታ እና በነቢዩ መካከል የነበረ ውይይት ነው። በምዕራፍ ፪ ውስጥ ጌታ ዕንባቆምን ትዕግስተኛ እንዲሆን መከረው—ጻድቅ ሰው በእምነት ለመኖር ይማራል። ምዕራፍ ፫ የእግዚአብሔርን ፍትህ የተቀበለበትን የዕንባቆምን ጸሎት መዝግቧል።