ገንዘብ ደግሞም ሀብቶች; ምፅዋት፣ የምፅዋት ስጦታ; አለማዊነት; አስራት፣ አስራት መክፈል ተመልከቱ ሰዎች ለእቃ ወይም ለአገልግሎት ለመክፈል የሚጠቀሙበት ሳንቲም፣ ወረቀት፣ የምስክር ወረቀት ወይም አንድ ነገር። ይህም አንዳንዴ የነገር ወዳጅነት ምሳሌ ነው። ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ, ኢሳ. ፶፪፥፫. አስራ ሁለቱ ለመንገድ እንጀራም ቢሆን ከረጢትም ቢሆን መሐለቅም በመቀነታቸው ቢሆን እንዳይዙ ተነገራቸው, ማር. ፮፥፰. ጴጥሮስ ጠንቋዩ ስምዖንን ገንዘቡ ከእርሱ ጋር እንደሚጠፋ ነገረው, የሐዋ. ፰፥፳. ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነው, ፩ ጢሞ. ፮፥፲. ዋጋ በሌለው ነገር ገንዘብ አታባክኑ, ፪ ኔፊ ፱፥፶–፶፩ (ኢሳ. ፶፭፥፩–፪; ፪ ኔፊ ፳፮፥፳፭–፳፯). ለገንዘብ ከሰሩ ይጠፋሉ, ፪ ኔፊ ፳፮፥፴፩. ሀብትን ከመፈለጋችሁ በፊት፣ የእግዚአብሔርን መንግስት ፈልጉ, ያዕቆ. ፪፥፲፰–፲፱. ቤተክርስቲያናት በገንዘባችሁም ኃጢአታችሁ ይቅር ይባልላችኋል ይላሉ, ሞር. ፰፥፴፪፣ ፴፯. ለፅዮን ምክንያት ገንዘቡን የሚሰጥ በምንም ዋጋውን አያጣም, ት. እና ቃ. ፹፬፥፹፱–፺.