የተቀባው ደግሞም መሲህ; ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ ኢየሱስ ክርስቶስ (የግሪክ ቃል) ወይም መሲሕ (የአራሜይክ ቃል) ተብሎ ተጠርቷል። ሁለቱም ቃላቶች “የተቀባው” ማለት ናቸው። የሰው ዘርን ደህንነት በሚመለከት በሁሉም ነገሮች የአብ ወኪል እንዲሆን በአብ የተቀባው እርሱ ነው። እግዚአብሔር ቀብቶኛልና, ኢሳ. ፷፩፥፩–፫. ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ቀብቶታል, ሉቃ. ፬፥፲፮–፳፪. ኢየሱስ በ እግዚአብሔር አብ ተቀብቷል, የሐዋ. ፬፥፳፯. እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስ ቀባው, የሐዋ. ፲፥፴፰.