የጋራ ስምምነት
የቤተክርስቲያን አባላት በቤተክርስቲያኗ እንዲያገለግሉ የተጠሩትን፣ እንዲሁም ድጋፋቸው የሚያስፈልገው ለሎች የቤተክርስቲያን ውሳኔዎችን የሚደግፉባቸው መሰረታዊ መመሪያ ነው፣ በብዙም ጊዜ ይህ የሚታየው የቀኝ እጅን በማንሳት ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተክርስቲያኑ መሪነት ይቆማል። በመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት በኩልም የቤተክርስቲያን መሪዎቹን በአስፈላጊ ስራዎች እና ውሳኔዎች ላይ መመሪያ ይሰጣቸዋል። ነገር ግን፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት ሁሉ የመሪዎችን ስራዎችና ውሳኔዎች የመደገፍ ወይም ያለመደገፍ መብትና እድል አላቸው።