መልስ መስጠት፣ ሂሳብ፣ ተጠያቂነት፣ ሀላፊነት ደግሞም ነጻ ምርጫ ተመልከቱ ጌታ ሁሉም ሰዎች ለእራሳቸው ምክንያቶች፣ ጸባያት፣ ፍላጎቶች፣ እና ስራዎች ሀላፊ ናቸው አለ። የተጠያቂነት እድሜ ልጆች ለእራሳቸው ስራዎች ሀላፊ እንደሆኑ እና ኃጢያት ለመስራት እና ንስሀ ለመግባት ችሎታ እንዳላቸው የሚታሰቡበት እድሜ ነው። እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ, ሕዝ. ፲፰፥፴. ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል, ማቴ. ፲፪፥፴፮. የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ, ሉቃ. ፲፮፥፪. እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን, ሮሜ ፲፬፥፲፪. ሙታን እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ, ራዕ. ፳፥፲፪. ቃላቶቻችን፣ ስራዎቻችን፣ እና ሀሳቦቻችን ይፈርዱብናል, አልማ ፲፪፥፲፬. መልካምም ይሁን መጥፎ ለማድረግ በራሳችን ላይ ፈራጅ እንሆናለን, አልማ ፵፩፥፯. ለራሳችሁ እንድትሰሩ ተፈቅዶላችኋል, ሔለ. ፲፬፥፳፱–፴፩. ይህንን ነገር እንድታስተምር እልሃለሁ—ሊጠየቁበት ለሚችሉ ንሰሃ እና ጥምቀት እንደሚያስፈልጋቸው, ሞሮኒ ፰፥፲. ለተጠያቂነት እድሜ የደረሱ ሁሉ ንሰሃ መግባት እና መጠመቅ አለባቸው, ት. እና ቃ. ፲፰፥፵፪. ተጠያቂ እስኪሆኑ ድረስ ህጻናት ልጆችን ለመፈተን ሰይጣን አይችልም, ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፮–፵፯. ልጆች በስምንት አመታቸው ይጠመቁ, ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፯. እያንዳድኑም ሰው ለእራሱ ኀጥያቶች በፍርድ ቀን ተጠያቂ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፻፩፥፸፰. ጥሩ ከመጥፎ እንዲያውቁም ተሰጥቶአቸዋል፤ ስለዚህ ለእራሳቸው ሃላፊ ናቸው, ሙሴ ፮፥፶፮. ሰዎች ለእራሳቸው ኃጥያቶች ይቀጣሉ, እ.አ. ፩፥፪.