የጥናት እርዳታዎች
ያዕቆብ፣ የዘብዴዎስ ልጅ


ያዕቆብ፣ የዘብዴዎስ ልጅ

በምድራዊ አገልግሎቱ ጊዜ ኢየሱስ ከመረጣቸው አስራ ሁለት ሐዋሪያት መካከል አንዱ ከወንድሙ ዮሐንስ ጋር የተመረጠ ነበር። በአንዳንድ ልዩ ጊዜዎች ከኢየሱስ ጋር እንዲሆኑ ከተመረጡት ሶስት ሐዋሪያት አንዱ፥ በኢያኢሮስ ሴት ልጅ ከሞት መነሳት ጊዜ (ማር. ፭፥፴፯)፣ በመለወጥ ጊዜ (ማቴ. ፲፯፥፩ማር. ፱፥፪ሉቃ. ፱፥፳፰)፣ እና በጌቴሴማኒ (ማቴ. ፳፮፥፴፯ማር. ፲፬፥፴፫)። ከጴጥሮስ እና ከዮሐንስ ጋር ጆሴፍ ስሚዝን እና ኦሊቨር ካውደሪን በመሾም፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ወደ ምድር በዳግም መለሰ (ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፪፻፳፰፥፳ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፸፪)።