ኤጲስ ቆጶስ ደግሞም አሮናዊ ክህነት ተመልከቱ “አለቃ”፣ የሀላፊነት ስፍራ ወይም ስልጣን ማለት ነው። ኤጲስ ቆጶስ በአሮናሚ ክህነት ውስጥ የተሾመ ሀላፊነት ነው (ት. እና ቃ. ፳፥፷፯፤ ፻፯፥፹፯–፹፰)፣ እና ኤጲስ ቆጶስ የእስራኤል ዋና ዳኛ ነው (ት. እና ቃ. ፻፯፥፸፪፣ ፸፬)። መንፈስ ቅዱስ እናንተን አልቃ አድርጓል, የሐዋ. ፳፥፳፰. የኤጲስ ቆጶሳት የመሆን ብቃት ተዘርዝረዋል, ፩ ጢሞ. ፫፥፩–፯ (ቲቶ ፩፥፯). ኤጲስ ቆጶስ ይሾም, ት. እና ቃ. ፳፥፷፯. ኤድዋርድ ፓርትሪጅ እንደ ቤተክርስቲያኗ ኤጲስ ቆጶስ ሊያገለግል ነበር, ት. እና ቃ. ፵፩፥፱. ኤጲስ ቆጶስ የመንፈስ ስጦታዎችን ይገንዘብ, ት. እና ቃ. ፵፮፥፳፯፣ ፳፱. ሊቀ ካህን በኤጲስ ቆጶስ ሀላፊነት ለማስተዳደር ይችላል, ት. እና ቃ. ፷፰፥፲፬፣ ፲፱ (ት. እና ቃ. ፻፯፥፲፯). ኤጲስ ቆጶስ በጌታ የተመደበ ነው, ት. እና ቃ. ፸፪. ኤጲስ ቆጶስ ደሀዎችን ይንከባከብ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፻፲፪. ኤጲስ ቆጶስ ስጋዊ ነገሮችን ሁሉ ያስተዳድር, ት. እና ቃ. ፻፯፥፷፰. ኤጲስ ቆጶስ የአሮናዊ ክህነት ፕሬዘደንት ነው, ት. እና ቃ. ፻፯፥፹፯–፹፰.