የመጀመሪያው ፍሬዎች በዘመን የሚሰበሰብ የመጀመሪያው አዝመራ። በብሉይ ኪዳን ዘመናት፣ እነዚህ ለጌታ ቀርበው ነበር (ዘሌዋ. ፳፫፥፱–፳)። ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያ ከሞት የተነሳ ስለሆነ ለእግዚአብሔር የመጀመሪያው አዝመራ ነው (፩ ቆሮ. ፲፭፥፳፣ ፳፫፤ ፪ ኔፊ ፪፥፱)። ወንጌልን የተቀበሉ እና እስከ መጨረሻ በታማኝነት የጸኑ፣ የእግዚአብሔር ስለሆኑ፣ በምሳሌነት የመጀመሪያ ፍሬዎች ናቸው። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት ለእግዚአብሔር በኵራት ናቸው, ራዕ. ፲፬፥፬. መጀምሪያ ከእርሱ ጋር የሚወርዱት፣ የመጀመሪያ ፍሬዎች ናቸው, ት. እና ቃ. ፹፰፥፺፰.