መንፈሳዊ ስጦታ ደግሞም ቤተመቅደስ፣ የጌታ ቤት ተመልከቱ በአጠቃላይ አስተሳሰብ፣ የእግዚአብሔር ሀይል ስጦታ። ብቁ የቤተክርስቲያኗ አባላት ዘለአለማዊነትን ለማግኘት የሚያስፈልጋቸውን መመሪያና የቅዱስ ክህነት ቃል ኪዳኖች በሚሰጣቸው በቤተመቅደስ ስነስርዓቶች በኩል የሀይል ስጦታን ይቀበላሉ። መንፈሳዊ ስጦታ ስለደህናነት አላማ መመሪያንም ይጨምራል። በእዚያም ከላይ የኃይል መንፈሳዊ ስጦታም ይሰጣችኋል, ት. እና ቃ. ፴፰፥፴፪፣ ፴፰ (ሉቃ. ፳፬፥፵፱; ት. እና ቃ. ፵፫፥፲፮). ቤት ገንቡ፣ በዚህ ቤትም የመረጥኳቸውን ከላይ መንፈሳዊ ስጦታ ለመስጠት አቅጃለሁ, ት. እና ቃ. ፺፭፥፰. ታላቅ መንፈሳዊ ስጦታ እና በረከት አዘጋጅቻለሁ, ት. እና ቃ. ፻፭፥፲፪፣ ፲፰፣ ፴፫. አገልጋዮቼ በተቀበሉት መንፈሳዊ ስጦታ ምክንያት የብዙዎች ልብ በታላቅ ይደሰታሉ, ት. እና ቃ. ፻፲፥፱. ግርማ፣ ክብር፣ እና መንፈሳዊ ስጦታ፣ በቅዱስ ቤቴ ስነስርዓት የተሾሙ ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፴፱. በአብ እንደ አሮን የተጠሩ በክህነት ስልጣን ቁልፎች ይበለፅጋሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፶፱.