ጥበብ ደግሞም ማስተዋል; እውቀት; እውነት ተመልከቱ በትክክል ለመፍረድ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ችሎታ ወይም ስጦታ። ሰው ጥበብን የሚያገኘው በአጋጣሚና በማጥናት እእንዲሁም የእግዚአብሔርን ምክር በመከተል ነው። ያለ እግዚአብሔር እርዳታ፣ ሰው እውነተኛ ጥበብ አይኖረውም (፪ ኔፊ ፱፥፳፰፤ ፳፯፥፳፮)። እግዚአብሔርም ለሰሎሞን ጥበብ ሰጠው, ፩ ነገሥ. ፬፥፳፱–፴. ጥበብ መሰረታዊ መመሪያ ነው፥ ጥበብ አግኝ, ምሳ. ፬፥፯. ጥበብን የሚያገኝ ነፍሱን ይወድዳል, ምሳ. ፲፱፥፰. ኢየሱስ በጥበብ ጠነከረ, ሉቃ. ፪፥፵፣ ፶፪. ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ እግዚአብሔርን ይለምን, ያዕ. ፩፥፭ (ት. እና ቃ. ፵፪፥፷፰; ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፲፩). እናንተ ጥበብን ትማሩ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እናገራችኋለሁ, ሞዛያ ፪፥፲፯. በጎልማሳነትህ ዘመን ጥበብን ተማር, አልማ ፴፯፥፴፭. ቅዱሳን ጥበብ እና ታላቅ የእውቀት ሀብት ያገኛሉ, ት. እና ቃ. ፹፱፥፲፱. ደንቆሮውም እራሱን ትሁት በማድረግ እና ጌታ አምላኩን በመጥራት ጥበብን ይማር, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፴፪.