የእግዚአብሔር ትእዛዛት ደግሞም ህግ; ታዛዥነት፣ ታዛዥ፣ መታዘዝ; ኃጢያት; አስሩ ቃላት; የእግዚአብሔር ቃል ተመልከቱ። በግል ወይም ለሁሉም የተሰጡ ህግጋት እና እግዚአብሔር በሰው የሚፈልጋቸው ነገሮች። ትእዛዛትን መጠበቅ ለታዛዦች የጌታን በረከቶች ያመጥል (ት. እና ቃ. ፻፴፥፳፩)። ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ, ዘፍጥ. ፮፥፳፪. በሥርዓቴ ብትሄዱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉትም, ዘሌዋ. ፳፮፥፫. ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ, ምሳ. ፬፥፬ (ምሳ. ፯፥፪). ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ, ዮሐ. ፲፬፥፲፭ (ት. እና ቃ. ፵፪፥፳፱). ትእዛዙንም የምንጠብቅ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን, ፩ ዮሐ. ፫፥፳፪. ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም, ፩ ዮሐ. ፭፥፫. ትዕዛዝ በመጠበቅ ጠንካራ፣ ፅኑና፣ የማትነቃነቅ ሁኑ, ፩ ኔፊ ፪፥፲. ጌታ ለማሟላት መንገድ ካላዘጋጀ በቀር ትእዛዛት አይሰጥም, ፩ ኔፊ ፫፥፯. በእግዚአብሔር ጥብቅ ትዕዛዝ መሰረት ማድረግ አለብኝ, ያዕቆ. ፪፥፲. ትእዛዛቴን እስከጠበክ ድረስ በምድሯ ትበለፅጋለህ, ጄረም ፩፥፱ (አልማ ፱፥፲፫; ፶፥፳). በወጣትነትህ ትእዛዛትን ለማክበር ተማር, አልማ ፴፯፥፴፭. እነዚህ ትእዛዛት ከ እኔ ናቸው, ት. እና ቃ. ፩፥፳፬. ትእዛዛትን መርምሩ, ት. እና ቃ. ፩፥፴፯. ትእዛዛትን የማይጠብቁ ሊድኑ አይችሉም, ት. እና ቃ. ፲፰፥፵፮ (ት. እና ቃ. ፳፭፥፲፭; ፶፮፥፪). ትእዛዛት የሚሰጡት የጌታን ፈቃድ እንድንረድ ነው, ት. እና ቃ. ፳፱፥፴፭. ትእዛዛት የሚሰጡት የጌታ ፈቃድ እንዲገባን ነው, ት. እና ቃ. ፹፪፥፰. እግዚአብሔር ስላዘዘኝ እንጂ፣ ለምን እንደሆነ አላውቅም, ሙሴ ፭፥፮. እና ጌታ አምላክ የሚያዛቸውን ማንኛቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን, አብር. ፫፥፳፭.