ምስክር ደግሞም ምስክርነት ተመልከቱ አንድ ነገር እውነት እንደሆነ መረጃ መስጠት። ምስክርም በግል እውቀት እንደዚህ አይነት መረጃን የሚሰጥ ሰውም ሊሆን ይችላል፤ ይህም ማለት ምስክር የሚሰጥ ነው። በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር, ዘፀአ. ፳፥፲፮. ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል, ማቴ. ፳፬፥፲፬ (ጆ.ስ.—ማቴ. ፩፥፴፩). ምስክሮቼ ትሆናላችሁ, የሐዋ. ፩፥፰. ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል, ሮሜ ፰፥፲፮ (፩ ዮሐ. ፭፥፮). ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን ቁሙ, ሞዛያ ፲፰፥፰–፱. ቅዱሣት መጻህፍትን የምንወስደው ሁልጊዜ ትእዛዛቱን ለማክበር እና ኢየሱስን ሁልጊዜ እንድናስታውስ ዘንድ ነው, ፫ ኔፊ ፲፰፥፲–፲፩ (ሞሮኒ ፬–፭; ት. እና ቃ. ፳፥፸፯–፸፱). እምነታችሁ እስከሚፈተን ድረስ ምስክርነትን አትቀበሉም, ኤተር ፲፪፥፮. የምስክሮች ህግ፥ በሁለት ወይም በሶስት አፍ ምስክርነት ሁሉም ቃል ይጸናል, ት. እና ቃ. ፮፥፳፰ (ዘዳግ. ፲፯፥፮; ማቴ. ፲፰፥፲፮; ፪ ቆሮ. ፲፫፥፩; ኤተር ፭፥፬; ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፫). ሐዋሪያት ትሆኑ እናም የስሜ ልዩ ምስክር እንድትሆኑ ሾምኳችሁ, ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፪ (ት. እና ቃ. ፻፯፥፳፫). ፳፭ ሰባዎቹ ለአህዛብና በአለም በሙሉ ልዩ ምስክሮች እንዲሆኑ ተጠርተዋል, ት. እና ቃ. ፻፯፥፳፭. መዝጋቢ ይኑር፣ እና እርሱም ለጥምቀቶቻችሁ የአይን ምስክር ይሁን, ት. እና ቃ. ፻፳፯፥፮ (ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፪–፬).