አስራት፣ አስራት መክፈል ደግሞም በኩራት; ገንዘብ ተመልከቱ በቤተክርስቲያን በኩል ለጌታ የሚሰጥ የሰው በአመት አንድ አስረኛ እድገት። የአስራት ገንዘቦች ቤተክርስቲያናትን እና ቤተመቅደሶችን ለመገንባት፣ የሚስዮን ስራን ለመደገፍ፣ እና የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ለመገንባት ይጠቀሙባቸዋል። አብርሐም የንብረቱን ሁሉ አስራት ለመልከ ጼዴቅ ሰጠ, ዘፍጥ. ፲፬፥፲፰–፳ (ዕብ. ፯፥፩–፪፣ ፱; አልማ ፲፫፥፲፭). የምድርም አሥራት ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው, ዘሌዋ. ፳፯፥፴–፴፬. ከዘርህ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣለህ, ዘዳግ. ፲፬፥፳፪፣ ፳፰. የሁሉንም አሥራት አብዝተው አቀረቡ, ፪ ዜና ፴፩፥፭. ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው, ሚል. ፫፥፰–፲፩ (፫ ኔፊ ፳፬፥፰–፲፩). አስራትን የሚከፍልም በሚመጣበት ጊዜ አይቃጠልም, ት. እና ቃ. ፷፬፥፳፫ (ት. እና ቃ. ፹፭፥፫). የጌታ ቤት በህዝቦቹ አስራት ይሰራ, ት. እና ቃ. ፺፯፥፲፩–፲፪. ጌታ የአስራት ህግን ገለጸ, ት. እና ቃ. ፻፲፱. አስራት በሸንጎ ይከፋፈላል, ት. እና ቃ. ፻፳.