ብቁ፣ ብቁነት ደግሞም ጻድቅ፣ ጽድቅ ተመልከቱ በግል ጻድቅ መሆን እና በጌታ እና በእርሱ በተመደቡት መሪዎች አስተያየት ተቀባይነትን ማግኘት። መስቀሉንም የማይዝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም, ማቴ. ፲፥፴፰. ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል, ሉቃ. ፲፥፯ (ት. እና ቃ. ፴፩፥፭). ብቁ ሳትሆኑ እንዳትጠመቁም ተጠንቀቁ, ሞር. ፱፥፳፱. ብቁ የሆኑ ካልሆነ በስተቀር እነርሱ አይጠመቁም, ሞሮኒ ፮፥፩. ስራ ፈት የሆነውም ለመቆም ብቁ ሆኖ አይቆጠርም, ት. እና ቃ. ፻፯፥፻. መገሰፅን ለመቀበል የማይችል ለመንግስቴ ብቁ አይደለም, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፴፩. ክህነት ብቁ ለሆኑ ወንድ አባላት በሙሉ ተሰጥቷል, አ.አ. ፪.