ኔፊ፣ የሔለማን ልጅ ደግሞም ሔለማን፣ የሔለማን ልጅ; ሌሂ፣ የኔፋውያን ሚስዮን ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ ታላቅ ኔፋውያን ነቢይና ሚስዮን። የሔለማን ታላቅ ልጅ ነበር, ሔለ. ፫፥፳፩. ዋና ዳኛ እንዲሆን ተመደበ, ሔለ. ፫፥፴፯. እርሱና ወንድሙ ሌሂ ብዙ ላማናውያንን ወደ ወንጌል አመጣቸው, ሔለ. ፭፥፲፰–፲፱. በእሳት ተከበበ እናም ከእስር ቤት ተለቀቀ, ሔለ. ፭፥፳–፶፪. በአትክልት ስፍራ ግንብ ላይ ጸለየ, ሔለ. ፯፥፮–፲. የዋና ዳኛውን መገደል ገለጸ, ሔለ. ፰፥፳፭–፳፰፤ ፱፥፩–፴፰. በጌታ ሀይል ተሰጠው, ሔለ. ፲፥፫–፲፩. ጌታ ረሃብን እንዲያመጣ እና ረሀብ እንዲቆም ጠየቀ, ሔለ. ፲፩፥፫–፲፰.