የሐዋርያት ስራ
ለቴዎፍሎስ ሉቃስ የጻፈው ከሁለት ክፍል ስራ ይህ መፅሐፍ ሁለተኛው ነው። የመጀመሪያው ክፍል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው ተብሎ ይታወቃል። ምዕራፍ ፩–፲፪ ከአዳኝ ሞት እና ትንሳኤ ወዲያው በጴጥሮስ አመራር በኩል የነበሩትን የአስራ ሁለት ሐዋሪያት አንዳንድ ታላቅ የሚስዮን ስራዎችን ይመዘግባል። ምዕራፍ ፲፫–፳፰ የሐዋሪያው ጳውሎስን አንዳንድ ጉዞዎች እና የሚስዮን ስራዎችን ይዘረዝራል።