የጥፋት ልጆች
ከእርሱ ጋር ለዘለአለም የሚሰቃዩ የሰይጣን ተከታዮች። የጥፋት ልጆች በተጨማሪም (፩) ሰይጣንን የተከተሉት እና ከምድረ ህይወት በፊት ከሰማይ በአመፅ ምክንያት ተጥለው የወጡት (፪) ወደ ዚህ አለም በስጋ ሰውነት እንዲወለዱ የተፈቀደላቸው ነገር ግን ከእዚያም በኋላ ሰይጣንን ያገለገሉ እና በእግዚአብሔር ላይ ያመጹት ናቸው። በእዚህ በሁለተኛው ቡድን ውስጥ ያሉት ከሞት ይነሳሉ ነገር ግን ከሁለተኛው (መንፈሳዊ) ሞት አይቤዡም እናም በክብር መንግስት ውስጥ ለመኖር አይችሉም (ት. እና ቃ. ፹፰፥፴፪፣ ፴፭)።