ከንቱ፣ ከንቱነት ደግሞም አለማዊነት; ኩራት ተመልከቱ ውስልት ወይም ውሸት፤ ኩራት ወይም ትዕቢት። ከንቱ እና ከንቱነት ደግሞም ባዶ ወይም ምንም ዋጋ የሌለው ማለት ሊሆንም ይችላል። ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ በጌታ ቅዱስ ቦታ ላይ ይቆማል, መዝ. ፳፬፥፫–፬. ስትጸልዩ በከንቱ አትድገሙ, ማቴ. ፮፥፯. ከንቱ ሀሳብ እና ኩራት ትልቅ አስፈሪ ገደል ነው, ፩ ኔፊ ፲፪፥፲፰. ልባችሁን በከንቱ ምድራዊ ነገሮች እንዲሁም በሀብት ላይ ማድረጋችሁን አሁንም ትቀጥላላችሁን, አልማ ፭፥፶፫. የዚህን ዓለም ከንቱ ነገሮች አትፈልግ፤ ከአንተም ጋር ይዘሀቸው ለመሄድ አትችልም, አልማ ፴፱፥፲፬. ከንቱነት እና ያለማመን ቤተክርስቲያኗን ሁሉ በፍርድ ላይ አድርገዋታል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፶፬–፶፭. ኩራታችንን ከንቱ ፍላጎታችንን ለማርካት ስንሞክር፣ ሰማያት እራሳቸውን ይለያሉ, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፴፯.