ታማኝ፣ ታማኝነት ደግሞም ቅንነት ተመልከቱ ልባዊ፣ እውነተኛና፣ ሀሰት የለሽ መሆን። እውነትን የሚያደርጉ ግን በጌታ ዘንድ የተወደዱ ናቸው, ምሳ. ፲፪፥፳፪. የተሳልኸውን ፈጽመው, መክ. ፭፥፬–፭. የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናል, ፪ ቆሮ. ፬፥፩–፪. ኑሮአችሁ መልካም ይሁን, ፩ ጴጥ. ፪፥፲፪. ለውሸታም ወዮለት፣ ወደታች ወደ ሲዖል ይጣላልና, ፪ ኔፊ ፱፥፴፬. መንፈስ እውነቱን ይናገራል እንጂ አይዋሽም, ያዕቆ. ፬፥፲፫. ማንም ከጎረቤቱ የተበደረ፣ የተበደረውን ነገር መመለስ አለበት, ሞዛያ ፬፥፳፰ (ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፳፭). ለሰዎች ፍትሃዊ ሁን፣ በትክክል ፍረድ፣ እናም ያለማቋረጥ መልካምን ስራ, አልማ ፵፩፥፲፬. እያንዳንዱም ሰው በቅንነት ይስራ, ት. እና ቃ. ፶፩፥፱. በመካከላቸው በልቦቻቸው ታማኝ እንደሆኑ የሚያውቁ፣ በእኔ ተቀባይ ናቸው, ት. እና ቃ. ፺፯፥፰. ታማኝ፣ ጥበበኛ፣ እና ጥሩ ሰዎች ለፖለቲካ ሀላፊነት ይፈለጉ, ት. እና ቃ. ፺፰፥፬–፲. ጎረቤታችሁ ያጡት ነገር ካገኛችሁ፣ እንደገና መልሳችሁ ለመስጠት በትጋት ፈልጉት, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፳፮. በታማኝነት እናምናለን, እ.አ. ፩፥፲፫.