ታዛዥነት፣ ታዛዥ፣ መታዘዝ ደግሞም ህግ; መራመድ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መራመድ (መሄድ); መባረክ፣ የተባረከ፣ በረከት; ማዳመጥ; የእግዚአብሔር ትእዛዛት; ደስታ ተመልከቱ በመንፈሳዊ አስተያየት፣ ታዛዥነት የእግዚአብሔር ፍላጎትን ማድረግ ነው። ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ, ዘፍጥ. ፮፥፳፪. አብርሐም ለጌታ ታዛዥ ሆነ, ዘፍጥ. ፳፪፥፲፭–፲፰. እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን, ዘፀአ. ፳፬፥፯. እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ይህን ታደርጋት ዘንድ ጠብቅ, ዘዳግ. ፮፥፩–፫. እግዚአብሔርን ትወድደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ, ዘዳግ. ፴፥፳. መታዘዝ ከመሥዋዕት ይበልጣል, ፩ ሳሙ. ፲፭፥፳፪. እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ, መክ. ፲፪፥፲፫–፲፬. በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ሁሉም ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም, ማቴ. ፯፥፳፩ (፫ ኔፊ ፲፬፥፳፩). ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ያውቃል, ዮሐ. ፯፥፲፯. ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል, የሐዋ. ፭፥፳፱. ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ, ኤፌ. ፮፥፩ (ቄላ. ፫፥፳). ጌታ ያዘዘኝንም ነገሮች በመሄድ አደርጋለሁ, ፩ ኔፊ ፫፥፯. የመንፈስ ድምፅ ታዛዥ እሆናለሁ, ፩ ኔፊ ፬፥፮–፲፰. የሰዎች ልጆች የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ከጠበቁ እርሱ ይመግባቸዋል, ፩ ኔፊ ፲፯፥፫. ለክፉ መንፈስ ታዛዥ እንዳትሆኑ ዘንድ ተጠንቀቁ, ሞዛያ ፪፥፴፪–፴፫፣ ፴፯ (ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፭). ሰዎች በሚታዘዙበት መንፈስ መሰረት ዋጋቸውን ይቀበላሉ, አልማ ፫፥፳፮–፳፯. ሰዎች በእራሳቸው ነጻ ፍላጎት ብዙ ነገሮችን ያድርጉ, ት. እና ቃ. ፶፰፥፳፮–፳፱. በሁሉም ነገሮች ውስጥ የእርሱ እጅ እንዳለበት ከማይመሰክሩ እና ትእዛዙን ከማያከብሩ በቀር፣ በምንም ሰው እግዚአብሔርን አያስቀይመውም፣ ወይም በማንም ላይ ቁጣው አይቀጣጠልም, ት. እና ቃ. ፶፱፥፳፩. እኔ ጌታ የምለውን ስታደርጉ እገደዳለሁ, ት. እና ቃ. ፹፪፥፲. ድምጼን የሚያከብር እያንዳንዱ ነፍስ ሁሉ ፊቴን ያያል እና እኔ እንደሆንኩም ያውቃል, ት. እና ቃ. ፺፫፥፩. ህዝቦቼ ታዛዥነት እስከሚማሩ ድረስ፣ መገሰፅ ያስፈልጋቸዋል, ት. እና ቃ. ፻፭፥፮. ከእግዚአብሔር ምንም በረከት ስናገኝ፣ ይህን የምናገኘው የተመሰረተበትን ህግ በማክበር ነው, ት. እና ቃ. ፻፴፥፳፩. አዳምም ታዛዥ ነበር, ሙሴ ፭፥፭. ጌታ አምላክ የሚያዛቸውን ማንኛቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን, አብር. ፫፥፳፭.