ርህራሄ ደግሞም ልግስና; መሀሪ፣ ምህረት; ፍቅር ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ርህራሄ ማለት “ከሌላ ጋር መሰቃየት” ማለት ነው። ደግሞም የሀዘን ተካፋይነትን፣ የሀዝን ስሜትን፣ እና ምህረትን ማሳየት ማለት ነው። ጌታ ህዝቡ ሩህሩህ እንዲሆኑ ጠራቸው, ዘካ. ፯፥፰–፲. ኢየሱስ አዘነላቸው, ማቴ. ፱፥፴፮ (ማቴ. ፳፥፴፬; ማር. ፩፥፵፩; ሉቃ. ፯፥፲፫). አንድ ሳምራዊ አዘነለት, ሉቃ. ፲፥፴፫. አንዳችሁ ለሌላችሁ ርኅሩኆችና ሁኑ, ፩ ጴጥ. ፫፥፰. ክርስቶስ ለሰዎች ልጆች በርህራሄ ይሞላል, ሞዛያ ፲፭፥፱. አንጀቴ ለእናንተ በርህራሄ ተሞልቷል, ፫ ኔፊ ፲፯፥፮. ጆሴፍ ስሚዝ ለጌታ ርህራሄ ጸለየ, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፫–፭.