ሞሮኒሀ፣ የሻንበል ሞሮኒ ልጅ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ጻድቅ የኔፋውያን አዛዥ (በ፷ ም.ዓ. አካባቢ)። ሞሮኒ ሞሮኒሀ ተብሎ ለሚጠራው ልጁ የሠራዊቱን መሪነት አሳልፎ ሠጠ, አልማ ፷፪፥፵፫. የዛራሔምላን ከተማ በድጋሚ ወሰደ, ሔለ. ፩፥፴፫. ኔፋውያን ንስሀ እንዲገቡ አደረገ እናም በምድር ግማሽ ላይ ቁጥጥርን በዳግም አገኘ, ሔለ. ፬፥፲፬–፳.