ሁለንተና ደግሞም ታዛዥነት፣ ታዛዥ፣ መታዘዝ ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ብዙ ጊዜ በጌታ ወይም በአገልጋዩ የተሰጠ ተግባር፣ የስራ ምደባ፣ ወይም ሀላፊነት። ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፣ ትእዛዙንም ጠብቅ, መክ. ፲፪፥፲፫. እግዚአብሔር ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ ነው, ሚክ. ፮፥፰. ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል, የሐዋ. ፭፥፳፱. ሀላፊነታቸውን እንዲያስታውሱ ለማነሳሳት በመቅሰፍት ተመተው ነበር, ሞዛያ ፩፥፲፯. የሽማግሌዎች የካህናት፣ የመምህራን፣ እና የዲያቆኖች ሀላፊነቶች ተገልጸዋል, ት. እና ቃ. ፳፥፴፰–፷፯. የክህነት ባለስልጣኖች የቤተሰብ ሀላፊነቶችን ሁሉ ያከናውኑ, ት. እና ቃ. ፳፥፵፯፣ ፶፩. ከጥምቀት በኋላ አባላት ያሏቸው ሀላፊነቶች ተገልጸዋል, ት. እና ቃ. ፳፥፷፰–፷፱. ህዝቦቼ ሀላፊነታቸውን በተመለከት በፍጹም እንዲማሩ ዘንድ ሽማግሌዎቼ ለጥቂት ዘመን ይጠብቁ, ት. እና ቃ. ፻፭፥፱–፲. እያንዳንዱ ሰው ሀላፊነቱን ይማር, ት. እና ቃ. ፻፯፥፺፱–፻.