ገነት ደግሞም ሰማይ ተመልከቱ ከዚህ ህይወት የሄዱ እና የሰውነት ትንሳኤን የሚጠብቁ ጻድቅ ነፍሳት የሚሄዱበት የመንፈስ አለም ክፍል ነው። ይህም የደስታ እና የሰላም ሁኔታ ነው። ገነት በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ የመንፈሶች አለምን (ሉቃ. ፳፫፥፵፫) ሰለስቲያል መንግስት (፪ ቆሮ. ፲፪፥፬)፣ እና በአንድ ሺህ አመት ምድር የምትገኝበትን የክብር ሁኔታን (እ.አ. ፩፥፲) ለመጠቆም ይጠቀሙበታል። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ, ራዕ. ፪፥፯. የእግዚአብሔር ገነት የቅዱሳንን መንፈስ ማስረከብ አለባት, ፪ ኔፊ ፱፥፲፫. የፃድቃኖች መንፈስ፣ ገነት ተብላ ወደምትጠራው፣ የእረፍት ቦታ ይገባሉ, አልማ ፵፥፲፩–፲፪. ከሦስቱ በስተቀር ሁሉም የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ወደ እግዚአብሔር ገነት ሄደዋል, ፬ ኔፊ ፩፥፲፬. በቅርብ ወደ እግዚአብሔር ገነት ለማረፍ እሄዳለሁ, ሞሮኒ ፲፥፴፬. ክርስቶስ ጻድቅ መንፈሶችን በገነት ውስጥ አገለገለ, ት. እና ቃ. ፻፴፰.