ልጅ፣ ልጆች ደግሞም መልስ መስጠት፣ ሂሳብ፣ ተጠያቂነት፣ ሀላፊነት; መባረክ፣ የተባረከ፣ በረከት—ልጆችን መባረክ; ቤተሰብ; የህጻን ጥምቀት; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; ደህንነት—የልጆች ደህንነት ተመልከቱ ወጣት ሰው፣ ጉልምስና ላይ ገና ያልደረሰ። አባቶች እና እናቶች ልጆቻቸውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲያከብሩ ያሰልጥኑአቸው። ልጆች የአቅመ አዳም እድሜ ላይ እስከሚደርሱ ድረስ ኃጢያት የላቸውም (ሞሮኒ ፰፥፳፪፤ ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፯)። ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው, መዝ. ፻፳፯፥፫–፭. ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው, ምሳ. ፳፪፥፮. ሕፃናትን ተዉአቸው፣ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው, ማቴ. ፲፱፥፲፬. ለወላጆቻችሁ ታዘዙ, ኤፌ. ፮፥፩–፫ (ቄላ. ፫፥፳). ያለውድቀት፣ አዳም እና ሔዋን ልጆች አይኖሯቸውም ነበር, ፪ ኔፊ ፪፥፳፪–፳፫. በእውነትና በጥሞና መንገድ እንዲራመዱ ልጆችን አስተምሯቸው, ሞዛያ ፬፥፲፬–፲፭. ትንንሽ ልጆች ዘለዓለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል, ሞዛያ ፲፭፥፳፭. ኢየሱስ ህፃናቶቻቸውን ወሰዳቸውና ባረካቸውም, ፫ ኔፊ ፲፯፥፳፩. እናም ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤ እናም የልጆችሽም ሰላም ታላቅ ይሆናል, ፫ ኔፊ ፳፪፥፲፫ (ኢሳ. ፶፬፥፲፫). ህጻናት ንስሀ መግባት እና መጠመቅ አያስፈልጋቸውም, ሞሮኒ ፰፥፰–፳፬. ህጻናት ከአለም መጀመሪያ ጀምሮ በአንድያ ልጄ ድነዋል, ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፮–፵፯. ወላጆች ልጆቻቸውን የወንጌል መሰረታዊ መርሆችን እና ስራዎችን ማስተማር ይገባቸዋል, ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፭፣ ፳፯–፳፰. ትንንሽ ልጆች በክርስቶስ ኃጢያት ክፍያ በኩል የተቀደሱ ናቸው, ት. እና ቃ. ፸፬፥፯. ወላጆች ልጆቻቸውን በብርሀን እና በእውነት እንዲያሳድጓቸው ታዝዘዋል, ት. እና ቃ. ፺፫፥፵. በተጠያቂነት እድሜዎች ከመድረሳቸው በፊት የሞቱት ልጆች በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ድነዋል, ት. እና ቃ. ፻፴፯፥፲.