እውነት ደግሞም ብርሀን፣ የክርስቶስ ብርሀን; እውቀተኛነት፣ እውቀተኛዎች; እውቀት ተመልከቱ ነገሮችን እንዳሉ፣ እናም እንደነበሩ፣ እናም እንደሚሆኑ ማወቅ (ት. እና ቃ. ፺፫፥፳፬)። እውነት ደግሞም ከሰማይ የሚመጣን ብርሀን እና ራዕይን ያጠቁማል። እውነት ከምድር በቀለች, መዝ. ፹፭፥፲፩ (ሙሴ ፯፥፷፪). እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል, ዮሐ. ፰፥፴፪. እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ, ዮሐ. ፲፬፥፮. ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም, ፩ ዮሐ. ፩፥፰. ጥፋተኞች እውነትን ከባድም አድርገው ይወስዱታል, ፩ ኔፊ ፲፮፥፪. ጻድቆች እውነትን ይወዳሉ, ፪ ኔፊ ፱፥፵. መንፈስ እውነቱን ይናገራል እንጂ አይዋሽም, ያዕቆ. ፬፥፲፫. አንተ የእውነት አምላክ ነህና፣ ለመዋሸት አትችልም, ኤተር ፫፥፲፪. የሁሉንም ነገር እውነታ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ታውቁታላችሁ, ሞሮኒ ፲፥፭. እውነት ለዘላለም እስከ ዘላለም ይኖራል, ት. እና ቃ. ፩፥፴፱. ፲በእውነት መንፈስ መረዳትን አግኝተሀል, ት. እና ቃ. ፮፥፲፭. መጽሐፈ ሞርሞን እውነትን እና የእግዚአብሔርን ቃል ይዟል, ት. እና ቃ. ፲፱፥፳፮. አፅናኚ እውነትን ለማስተማር ተልኳል, ት. እና ቃ. ፶፥፲፬. በእውነት መንፈስ በኩል ቃልን የሚቀበል የሚቀበለው በእውነት መንፈስ እንደሚሰበክ ነው, ት. እና ቃ. ፶፥፲፯–፳፪. በሰጠኋችሁ ራዕዮች በኩል እውነቶችን አውጁ, ት. እና ቃ. ፸፭፥፫–፬. እውነት የሆነውም ብርሀን ነው, ት. እና ቃ. ፹፬፥፵፭. የክርስቶስ ብርሀን የእውነት ብርሀን ነው, ት. እና ቃ. ፹፰፥፮–፯፣ ፵. መንፈሴም እውነት ነው, ት. እና ቃ. ፹፰፥፷፮. የመረዳት ችሎታ፣ ወይም የእውነት ብርሀን፣ የተፈጠረ አይደለም, ት. እና ቃ. ፺፫፥፳፱. የእግዚአብሔር ክብር የመረዳት ችሎታ ነው, ት. እና ቃ. ፺፫፥፴፮. ልጆቻችሁን በብርሀን እና በእውነት እንድታሳድጓቸው አዛችኋለሁ, ት. እና ቃ. ፺፫፥፵. አንድያ ልጄም በጸጋና በእውነት ተሞልቷል, ሙሴ ፩፥፮.