ማጠብ፣ የታጠበ፣ የሚታጠቡ ደግሞም የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; ጥምቀት፣ መጥመቅ ተመልከቱ በስጋዊ ወይም በመንፈሳዊ ማጽዳት። በምሳሌ፣ ንስሀ የገባ ሰው በኃጢያት እና በዚህ ውጤታ ሸከም ከነበረበት ህይወት በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት በኩል ለመጽዳት ይችላሉ። በትክክለኛው ክህነት በኩል የሚከናወኑ መታጠብ እንደ ቅዱስ ስነስርዓት ለማገልገል ይችላሉ። ካህኑም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል, ዘኁል. ፲፱፥፯. ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ, መዝ. ፶፩፥፪፣ ፯. ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ ክፉ ማድረግን ተዉ, ኢሳ. ፩፥፲፮–፲፰. ኢየሱስ የሐዋሪያቱን እግሮች አጠበ, ዮሐ. ፲፫፥፬–፲፭ (ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፴፰–፻፴፱). ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ, የሐዋ. ፳፪፥፲፮ (አልማ ፯፥፲፬; ት. እና ቃ. ፴፱፥፲). ማንም ሰው ልብሱ ነጭ ሆኖ ካልታጠበ በቀር መዳን አይችልም, አልማ ፭፥፳፩ (፫ ኔፊ ፳፯፥፲፱). በክርስቶስ ደም ልብሳቸው እስከሚነጣ ታጥበው ነበር, አልማ ፲፫፥፲፩ (ኤተር ፲፫፥፲). ትእዛዛትን በማክበርም ከኀጥያታቸው ሁሉ ይታጠቡ እና ይጽዱ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶፪. መቀባታችሁ፣ እና መታጠባችሁ፣ በቅዱስ ቤቴ ስነስርዓት የተሾሙ ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፴፱–፵፩.