ካሌብ ከስደት ከሁለት አመት በኋላ የከነዓንን ምድር እንዲፈትሽ በሙሴ ከተላኩት አንዱ። እርሱ እና ኢያሱ ብቻ ስለምድሩ እውነተኛ ሀተታ አመጡ (ዘኁል. ፲፫፥፮፣ ፴፤ ፲፬፥፮–፴፰)። ከግብፅ ከወጡት እነርሱ ብቻ በምድረበዳው ውስጥ ለአርባ አመታት ተረፉ (ዘኁል. ፳፮፥፷፭፤ ፴፪፥፲፪፤ ዘዳግ. ፩፥፴፮) እናም ወደ ከነዓን ገቡ (ኢያ. ፲፬፥፮–፲፬፤ ፲፭፥፲፫–፲፱)።