ምክር (ስም) ደግሞም ነቢይ ተመልከቱ ከጌታ እና ከተሾሙ መሪዎቹ የሚመጡ ግሰጻ፣ ማስጠንቀቂያ፣ ምክር፣ እና ትምህርት። እመክርሃለሁ, ዘፀአ. ፲፰፥፲፱. እግዚአብሔር በምክሩ መራኝ, መዝ. ፸፫፥፳፬. መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል, ምሳ. ፲፩፥፲፬. ፈሪሳውያንና ሕግ አዋቂዎች የእግዚአብሔርን ምክር ከራሳቸው ጣሉ, ሉቃ. ፯፥፴. የእግዚአብሔርን ምክር የሚያዳምጡ ከሆኑ መማር ጥሩ ነው, ፪ ኔፊ ፱፥፳፱. የሾማችሁን ምክር ስሙ, ት. እና ቃ. ፸፰፥፪. ከመደብኩት ምክር ተቀበሉ, ት. እና ቃ. ፻፰፥፩. ከመደብኩት ምክር በላይ የእራሱን ምክር ለመመስረት ተነሳስቷል, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፹፬. የአገልጋዬን ጆሴፍ ምክር አድምጡ, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፹፱. ማንም ሰው ምክሬን ካልፈለገ፣ ምንም ሀይል አይኖረውም, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፲፱.